ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

#አንተ_አባቴ_አይደለህም"

       "#አንተ#አባቴ#አይደለህም” ከገባሁበት የሃሣብ ባሕር የወጣሁት ኡስታዝ ሉቅማን ስለ አዕምሮ በሰጡን ተጨማሪ ትንታኔ ነበር። ኡስታዙ አዕምሮን ማዳበርና ከስሜት (emotion) በላይ እንዲውል ማሰልጠን ያለውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው ሲያስረዱን፡- “#አዕምሮን #በአግባቡ #አለመጠቀም #ስሜታዊና #ችኩል #ውሳኔዎች #እንድንወስን #ያደርገናል። የዳበረ አዕምሮ ያላቸው ስኬታማ ሰዎች በሚደርስባቸው ውጫዊ ጫና እና እነርሱ ለጫናው በሚሰጡት ምላሽ መካከል የማገናዘቢያ ጊዜ አላቸው፤ ድንገተኛና ችኩል ምላሽ አይሰጡም፤ ስለተፈጠረው ነገር ሙሉ መረጃ ሳይኖራቸው ለፍርድ አይሮጡም፤ ለውሳኔ አይቸኩሉም። ውሳኔያቸው ከዕውቀት እንጂ ከስሜት አይመነጭም። በስሜት ግፊት የተወሰነ ውሳኔ በአብዛኛው ከፍተኛ ጥፋት ያስከትላልና።” አሉ። ኡስታዙ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡ ከረጅም ጊዜ በፊት በአንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉ ምሁር ያቀረቡት አንድ አሳዛኝ ታሪክ ከላይ ያነሳሁላችሁን ሃሳብ ይበልጥ ግልፅ የሚያደርገው ይመስለኛል” አሉና ወደኛ ተመለከቱ። የዛሬውን ውይይትም በዚሁ ታሪክ እናሳርግ" አሉ የዕለቱን ፕሮግራም ለማገባደድ በማሰብ። ታሪኩን ለመስማት ያለንን ጉጉት ከሁኔታችን ተረድተዋል። ኡስታዙ ታሪኩን እንዲህ ሲሉ አወጉን፡- “ሰውየው ወደ ወህኒ ቤት የወረደው በጣም የምትወደውንና የሚወዳትን የትዳር አጋሩን ከአንድ ዓመት ሕፃን ልጁ ጋር በመተው ነበር። የአራት ዓመታት ጽኑ እሥራት ፍርደኛ ነው። እነኝህ ዓመታት ለባለቤቱ ፈታኝ ነበሩ። ቢሆንም በምትችለው አቅም ሁሉ የምታደርገውን እንክብካቤ አልቀነሰችም። ውድ ባለቤቷ ከእስሩ በላይ ሌላ ጭንቀት እንዳይፈጠርበት የአቅሟን ያህል ጥራለች። ምግብና ልብስ በማመላለስ ለባለቤቷ ያላት...

ካህሊል ጅብራን

  ካህሊል ጅብራን ተገዳይ በመገደሉ፣ተዘራፊውም በመዘረፍ ከክፉ ተግባራት የነፃ አይሆንም፣ ጥፋተኛውም የተበዳዩ ተጠቂ ነውና ይህንን ግዜ ከከተማው ዳኞች ኣንዱ ወደፊት ምጥቶ ቆመ፣ ኣለውም:- ስለ ወንጀልና ቅጣት ንገረን?" እርሱም እንዲህ ሲል መለሰለት:- በሌሎች ላይም ሆነ በእራሳችሁ ላይ ክፉ ስራ የሚትሰሩት መንፈሳችሁ በህዋው ውስጥ ሲዋልል ብቻችሁን ስትሆኑና ጠባቂ ሳይኖራቹ ስቀር ነው። ለዝያ ለተሰራ ሃጥያትም በቅዱሳን ደጅ ቆማቹ ማንም ሳያስተውላቹ በሩን ማንኳኳት እና ለጥቂት ግዜ መጠበቅ ይገባችኃል። ምክንያቱም ህሊናችሁ እንደ ውቅያኖስ ሰፊ ነውና። ሳይረክስም ለዘላለም ይቆያል........ ...ህሊና እንደ ሰማዩ ሁሉ ባለክንፎችን ብቻ ክፉ ኣድርጎ ያነሳል። ህሊናችሁ እንደ ፀሃይም ጭምር ነው። የፍልፈልን መንገዶችም አያውቅም። የእፍኝት ጉሬዎችንም አይፈልግም..... ይሁንና ህሊናቹ በውስጣቹ ብቻውን አይኖርም። በውስጣቹ ያለው አብዛኛው ክፍል ሰው ብሆንም የሚበዛው ኣሁንም ገና ሰው አልሆነም። ይሁንና በውስጣቹ የሚነቃበትን ግዜ ፍለጋ በእንቅልፍ ልቡ በጭጋግ ውስጥ የሚዘዋወር ቅርፀ ቢስ ድንክ ነው..... አሁንም መናገር የምፈቅደው በውስጣቹ ስላለው ሰው ነው..... ስለ ወንጀልና ስለወንጀል ቅጣትስ የሚያውቀው ያህሊናቹ ወይም ጭጋግ ውስጥ ያለው ድንክ ሳይሆን እርሱ እራሱ ውስጣችሁ አይደለምን?..... ብዙውን ግዜ ስለ ኣንድ በደልን የፈፀመ ሰው ስትናገሩ ሰውየው ከእናንተ ኣንዱ እንዳደለ ይልቅስ ለእናንተ እንግዳና ወደዓለማችሁ ዘው ብሎ የገባ ፍጡር እንደ ሆነ ኣድርጋቹ ስትናገሩ እሰማለው። እኔ ግን ቅዱሳንና ፃድቃንም ብሆኑ በያንዳንዳችሁ ውስጥ ካለው ከሁሉ ከፍ ከምለው ወጥተው ሊታዩ እንደ ማይችሉ ሁሉ ክፍዎችና ደካሞችም በውስጣችሁ ካለው ከሁሉ ...

100 BIRR

  #አይ #መቶ ብር .... አይይይይ መቶ ብር እንዲ መንምነህ እንገናኝ። እንደ መታወቅያ በኋላ ኪስ፣ እንደ ፎቶ በፍሬም አሽሞንሙነንህ እንዳላደግን አወዳደቅህ እንድህ ይሁን? ድሮኮ መቶ ብር እጅህ ሲገባ የምትገዛውን ነገር ስትዘረዝር ይደክመኃል። የአሁኑን ተው ገና ወዳንተ ሲመጣ አየር ላይ ያልቅና ልትሸምት ባሰብከው አስቤዛ ፋንታ ቀልድ ገዝተህ ትገባለህ..... ከዋና ስሟ ይልቅ ቅጥል ስሟ ተረፈን እኮ መቶ ብር። ከመቶ ብር ቅጢል ስሞች ሁሉ ግን የመጨረሻ አንጀቴን በሳቅ የበጠሰው ሰፊው ህዝብ የሚለው ነው። መቶ ብር ሰፊው ህዝብ ተብሏል አሉ። #ይሸጣል እንጂ #አይገዛም።      እያዩ ፈንገስ