"#አንዴ" #ኣንድ #ትልቅ #ፕሮፌሰር #ተወዳጅ #ዑስታዝ ከአንድ ተውዳጅ ታማሪው ጋር ግቢ ውስጥ ወክ ያደርጋሉ። እሄም ወክ ስላልበቃቸው ከዩኒቨርሲቲው ጀርባ ወዳሉ መንደሮች እንደገና ለመንቀሳቀስ ወሰኑ። ወሬዎቹን እየተጫወቱ ስለ ህይዎት መንገድ ቀጠሉ። ትንሽም እንደ ተጓዙ መንገድ ላይ ልብሶቹን አወላልቆ ቦት ጫማቸውን አውልቆ ስራ ሚሰራን የቀን ሰራተኛን ተመለከቱ። ከዝያ ወጣቱ ለመምህሩ፣ ምን ኣለው....ተመልከት እሄን ጫማ እኔ ሰርቀዋለው፣ እሄን ሰው ሰርቀውና ስራ ጨርሶ ዞር ሲል፣ጫማው ሲጠፋው እንዴት እንደምሆን ትመለከተዋለህ "እንስቃለን"ኣለው። እሄን ሲለው መምህሩ እሄን ወጣት የህይዎት ሜዳ ላይ ማስተማር የሚችልበት ጥሩ አጋጣሚ ኣገኘ። እችን ሀሳብ ቶሎ ለቀም ኣረጋትና፣ እንዲህ ብንገለብጠውስ አለው። እይታውን እየገለበጠለት ነው። ሰውየው ጫማው ጠፍቶት ሲጮህ ፣ሲያለቅስ፣ ሲጨነቅ አይተን ከምንስቅ፣ የሆኑ ሳንቲሞች ጫማው ውስጥ እንክተትና ሳያስበው ሳንቲሞቹን ስያወጣ፣ ሚፈጠርበትን ደስታ አይተን ብንስቅ አይሻልም? አለው። "ወጣቱ" ሀሳቡ እንግዳ ብሆንበትም ሀሳቡን ወደደው። ያንኛውን ተንኮል ሚመስለውን ስራ ኖሮበታል፣ ቅንነትን ነው ያልኖረበት፣ ልሞክረው ኣለ፣ እይታው እየተስተካከለ ነው። Attitudዱ እያደገ ነው እሄ ሰው። እሺ አለ፣ ኪስህ ስንት ኣለ አወጣጠ ሳንትሞች ብሮች፣ መምህሩም አወጡ ጫማው ውስጥ ጨመሩት። ከዚያም ራቅ ብሎ ጥላ ውስጥ ቁጭ ብለው ሰወየው ስራ እስኪጨርስ ጠበቁ። ሰውየውም ስራውን ጨረሰ፣ እጆቹን ታጠብ፣ እግሮቹን ታጠበ፣ ልብሱን ኣራገፍ፣ ያወለቀውን ልብስ ቀየረ፣ ኮፍያውን ደረበ ኣሁን ምን ቀረው? "ጫማው፣" ...ጫማውን ሊለብስ ብድግ አደረገና ድንገት የሆነ ነገር ገብቶበት...