http://seidahm.blogspot.com https://seidahm.blogspot.com/2024/05/blog-post.html https://t.me/WonderfulQoute/422 አንድ ሰው እንዲህ ሲል ልምምዱን ያካፍለናል፡- “ፈጣሪን ጥንካሬ እንዲሰጠኝ ጠየኩት፣ ፈጣሪም ጠንካራ የሚያደርጉኝን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሰጠኝ . . . 🌟ጥበብን እንዲሰጠኝ ጠየኩት፣ 👉እሱም የምፈታቸውን ችግሮች ሰጠኝ . . . 🌟ድፍረት እንዲሰጠኝ ጠየኩት፣ 👉እሱም ተጋፍጬ የማሸንፋቸውን አደገኛ ነገሮች ሰጠኝ . . . ❣️ፍቅርን እንዲጠኝ ጠየኩት፣ 👉እሱም እንድረዳቸው የተቸገሩ ሰዎችን ሰጠኝ . . . በጊዜው ግር ቢለኝም ጸሎቴ እንደተመለሰ የገባኝ የኋላ ኋላ ነው፡፡🙏🙏🙏 🙏 አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ካላችሁ፣ ጠንካራ ሆናችሁ እንደምትወጡ ላስታውሳችሁ፡፡ 🙏 ለመፍታት አስቸጋሪ የሆኑ ሁኔታዎች ከተደራረቡባችሁ፣ 🌟ጥበበኛ ወደመሆን እንደምታድጉ ላሳስባችሁ፡፡ 👉 የግድ አደገኛ ነገሮችን የመጋፈጥ ግዴታ ውስጥ የምታልፉ ከሆነ፣ 🙏ደፋርነት እያዳበራችሁ እንደምትሄዱ ጥርጥር አይግባችሁ፡፡ 👉በብዙ ችግር የተጎሳቆሉ ሰዎች እየተጠጓችሁ እንደሆነ ካያችሁ፣ ✍️የፍቅርና የርህራሄ ጉዳይ እየተለማመዳችሁ እንደምትሄዱ ትዝ ይበላችሁ፡፡☀️🌹🏵️ facebook.com/seidahmedH