ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከሜይ 10, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሰው እና ስርዓት

https://www.facebook.com/Seidtec/ ሰው የስርዓት ውጤት ነው፡፡ የሚያስበው በስርዓት ነው፡፡ ማንም ዝም ብሎ አያስብም፤ ዝም ብሎ ያስብ ዘንድ የተፈጠረ የለም፡፡ ሰው ለማሰቡ ሰበብ አለው፤ ለሃሳቡ ምክንያት አለው፡፡ ምክንያቱና ስርዓቱ ያመጣው ነው፡፡ ለማሰቡ መነሻ ሃሳብ ያስፈልገዋል፡፡ ከሰማው፣ ካየው፣ ከዳሰሰው፣ ከቀመሰው፣ ካሸተተው፣ ከነፍሱ ጥሪ፣ ከመንፈሱ ግፊት ተነስቶ ነው የሚያስበው፡፡ በል በል የሚለው ስሜት አለ፡፡ ያስብ ዘንድ የሚገፋፋው ውስጣዊ ግፊት አለ፡፡ እንዲያስብ የሚያደርገው ከአዕምሮው ጋር የተዋሃደ የሚንጠው ሃይል አለ፡፡ የሚከውነው በስርዓት ነው፡፡ ስርዓት ከልባችን ጋር ተጋምዷል፡፡ አፈጣጠራችን ራሱ ስርዓት አለው፡፡ መላው አካላችን በስርዓት ነው የሚሰራው፡፡ የልባችን አመታት፣ የኩላሊታችን አሰራር፣ የአዕምሯችን መዋቅር፣ የዲኤንኤያችን ድርድሮሽ፣ መላ አካላችን በስርዓት ነው የታነፀው፡፡ ሰው ከስርዓት ውጪ መሆን አይችልም፡፡ ሰማይና ምድሩ፣ ፀሐይና ጨረቃው፣ ባህርና የብሱ፣ ነፋሳቱና ዝናቡ፣ ወጀቡና ሞገዱ፣ የዓየር ንብረቱ ሁሉ በስርዓት ነው ስራውን የሚሰራው፡፡ https://www.facebook.com/Seidtec1990