ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ልጥፎችን ከመለያ https://www.Facebook.com/Seidtec41 ጋር በማሳየት ላይ

ጣቶቹ

ቆንጆ ነኝ ወይስ አይደለሁም? የሚል ጥያቄ ድንገት አእምሮዬ ውስጥ ብለጭ ያለው፣ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ ነበር፡፡ እስከዛሬም በየቀኑ፣ በየሰዓቱ፣ ጥያቄው በውስጤ ያቃጭላል፡፡ አንዳንዴ እንዲያውም የሆነ ሰው ጠርቼ “ለመሆኑ ቆንጆ ነኝ ወይስ _ አይደለሁም? ብዬ መጠየቅ ያምረኛል፡፡ የራሴን ፊት ማየት ናፍቄያለሁ:: የራሴን ፈገግታ፣ የራሴን ጥርሶች፣ የራሴን ከናፍርት፣ የራሴን ዓይኖችና አፍንጫ፤ ብቻ መልኬን ማየት ክፉኛ ፈልጌያለሁ፡፡ በጣም ፈልጌያለሁ፡፡ አንዳንዴ ፊቴን ሳስበው፣ የተጨማደደ ቆዳ፣ ብነካው ለእጄ እንደቆረቆንዳ የሚሻክር፣ ከንፈርና ግራ ጉንጨ ላይ የሚያዳልጥ፣ ስፋቱ ስሙኒ የሚያህል ጠባሳ የሚኖረው ይመስለኛል፡፡ ግን በቀኝ እጄ ጣቶች ፊቴን ስዳስሰው፣ የሚያጋጥመኝ ሌላ ነው፡፡ እንደተባዘተ ጥጥ የሚለሰልስ ቆዳ!! የቆዳዬ ልሰላሴ ለራሴም ይደንቀኛል፡፡ የፊቴ ቆዳ የእኔ አይመስለኝም፡፡ እጄ የሌላ ሰው ፊት ላይ ያረፈ ነው የሚመስለኝ፡፡ ታዲያ ከራሴ ቆዳ ጋር በፍቅር የወደቅሁ ይመስለኛል፡፡ ደጋግሜ የቀኝ እጄን መዳፍ፣ ጉንጨ ላይ በቀስታ አንሸራትተዋለሁ፤ ጣፋጭ ደስታ እንደማር በውስጤ ሲፈስ ይሰማኛል፣ ጣቶቼ ምላስ ሆነው የቆዳዬን ወለላ የቀመሱ ዓይነት፡፡ የዓይኔን ሽፋሽፍት የቅንድቤን ለስላሳ ጸጉር በጣቶቼ ስዳሰሳቸው የሚሰማኝ ሐሴት ወደር የለውም፡፡ መልኬን እንደ ብሬል ፅሁፍ በጣቴ ነበር የማነበው፡፡ ከራሴ ጋር ፍቅር የጀመረኝ፣ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ ነበር፡፡ ምንም ይሁን ምን፣ መኖር ጥሩ ነው! “መኖር ምናባቱ!” ብለን በገዛ ፈቃዳችን ነፍሳችንን ከሥጋችን ለመለየት ፈራ ተባ ስንል፤ ሕይወት የተሰፋ ቅንጥጣቢዋን በኑሮ ጎዳናችን ላይ እየጣለች፥ እንደ ለማዳ ውሻ ታስከትለናለች፡፡ እንጅማ ገና መቼና መቼ የሰው ልጅ እራሱን አጥፍቶ፣ ይችን ዓለም ዳዋ በወረሳት ...