ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 20, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#አንተ_አባቴ_አይደለህም"

       "#አንተ#አባቴ#አይደለህም” ከገባሁበት የሃሣብ ባሕር የወጣሁት ኡስታዝ ሉቅማን ስለ አዕምሮ በሰጡን ተጨማሪ ትንታኔ ነበር። ኡስታዙ አዕምሮን ማዳበርና ከስሜት (emotion) በላይ እንዲውል ማሰልጠን ያለውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው ሲያስረዱን፡- “#አዕምሮን #በአግባቡ #አለመጠቀም #ስሜታዊና #ችኩል #ውሳኔዎች #እንድንወስን #ያደርገናል። የዳበረ አዕምሮ ያላቸው ስኬታማ ሰዎች በሚደርስባቸው ውጫዊ ጫና እና እነርሱ ለጫናው በሚሰጡት ምላሽ መካከል የማገናዘቢያ ጊዜ አላቸው፤ ድንገተኛና ችኩል ምላሽ አይሰጡም፤ ስለተፈጠረው ነገር ሙሉ መረጃ ሳይኖራቸው ለፍርድ አይሮጡም፤ ለውሳኔ አይቸኩሉም። ውሳኔያቸው ከዕውቀት እንጂ ከስሜት አይመነጭም። በስሜት ግፊት የተወሰነ ውሳኔ በአብዛኛው ከፍተኛ ጥፋት ያስከትላልና።” አሉ። ኡስታዙ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡ ከረጅም ጊዜ በፊት በአንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉ ምሁር ያቀረቡት አንድ አሳዛኝ ታሪክ ከላይ ያነሳሁላችሁን ሃሳብ ይበልጥ ግልፅ የሚያደርገው ይመስለኛል” አሉና ወደኛ ተመለከቱ። የዛሬውን ውይይትም በዚሁ ታሪክ እናሳርግ" አሉ የዕለቱን ፕሮግራም ለማገባደድ በማሰብ። ታሪኩን ለመስማት ያለንን ጉጉት ከሁኔታችን ተረድተዋል። ኡስታዙ ታሪኩን እንዲህ ሲሉ አወጉን፡- “ሰውየው ወደ ወህኒ ቤት የወረደው በጣም የምትወደውንና የሚወዳትን የትዳር አጋሩን ከአንድ ዓመት ሕፃን ልጁ ጋር በመተው ነበር። የአራት ዓመታት ጽኑ እሥራት ፍርደኛ ነው። እነኝህ ዓመታት ለባለቤቱ ፈታኝ ነበሩ። ቢሆንም በምትችለው አቅም ሁሉ የምታደርገውን እንክብካቤ አልቀነሰችም። ውድ ባለቤቷ ከእስሩ በላይ ሌላ ጭንቀት እንዳይፈጠርበት የአቅሟን ያህል ጥራለች። ምግብና ልብስ በማመላለስ ለባለቤቷ ያላት...