ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከጁላይ 28, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አሌክስ አብረሃም

Seid Ahmed ከአስራ አንድ ዓመታት በፊት ደሀ ነበርን፡፡ ያጣን የነጣን፣ ሙልጭ ያልን ነጭ ድሆች. ከድህነታችን ከብደት የተነሳ ስንት ሰዓት ላይ እንደምንበላ ሳይሆን ስንት ሰዓት ላይ ርሀባች ጋብ እንደሚል ነበር ዘወትር የምናስበው፡፡ እኔና እህቴ ትምህርት ቤት፣ “አበበ በሶ ባላ የሚል ምሳሌ “ቲቸር' ሲናገሩ በመጎምጀት ምራቃችንን እንውጥ ነበር፡፡ ቤታችን ውስጥ አንድ የረገበ የሽቦ አልጋ፣ ሁለት የሳር ፍራሾችና አራት የተወላገዱ ኩርሲ ወንበሮች ብቻ እንደነበሩን ዛሬም ድረስ እናቴ ሳጥን ውስጥ ያሉት ታሪካዊ ፎቶዎች ያሳብቃሉ ፡፡ ግድግዳ ላይ ገና እንደተረገዝኩ የሞተ አባቴ ፎቶግራፍ የዘመን ጥቀርሻ እንዳወየበው በላስቲክ ተለብዶ ተሰቅሏል። እንግዲህ ቤታችን ሁለት ክፍል ነበረች፡፡ አሁን የነገርኳችሁ የሳሎናችንን (ወጉ እንዳይቀር ይዞታ ነው፡፡ ወደጓዳ ስትገቡ ውስጣቸው የእንጀራ ላስቲክ ብቻ ያለባቸው ሁለት ትልልቅና አሮጌ የእንጀራ መሶቦች ታገኛላችሁ፡፡ ጠርዛቸውን በደህና ቀን አይጥ የቸረቸፈው !! ሁለቱም ሁልጊዜ ባዶ ነበሩ (አይጦች ከልጆቻቸው ጋር በእነዚህ መሶቦች አጠገብ ሲያልፉ ለልጆቻቸው እንዲህ እያሉ ታሪክ የሚያወሩላቸው ይመስለኛል፡፡ “በድሮ ጊዜ በአያቶቻችን ዘመን፣ እነዚህ መሶቦች ውስጥ ተበልቶ የማያልቅ እንጀራ ነበር፡፡ የዛሬን አያድርገውና ለስንቱ የአይጥ ሰርግ ድግስ የበቃ - ወይ ጊዜ መሶብም እንደ ዓለማያ ሀይቅ ይደርቃል ! እናቴ ታዲያ አማኝ ናት፡፡ በየሦስት ቀኑ መሶቡ ውስጥ የሚቀመጡትን የእንጀራ ላስቲኮች እያጠበች አድርቃ ወደ መሶቡ ትመልሳቸዋለች፡፡ “በረከት ሲመጣ አዋጅ አያስነግርም፣ ድንገት ከተፍ ቢል ተዘጋጅተን መጠበቁ ደግ ነው” ትላለች፡፡ ይሄን መራር ስብከቷን አልወደውም - ግን ትንቢቷ ሰመረ፡፡ እናቴ ነብይ ነበረ...

ጣቶቹ

ቆንጆ ነኝ ወይስ አይደለሁም? የሚል ጥያቄ ድንገት አእምሮዬ ውስጥ ብለጭ ያለው፣ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ ነበር፡፡ እስከዛሬም በየቀኑ፣ በየሰዓቱ፣ ጥያቄው በውስጤ ያቃጭላል፡፡ አንዳንዴ እንዲያውም የሆነ ሰው ጠርቼ “ለመሆኑ ቆንጆ ነኝ ወይስ _ አይደለሁም? ብዬ መጠየቅ ያምረኛል፡፡ የራሴን ፊት ማየት ናፍቄያለሁ:: የራሴን ፈገግታ፣ የራሴን ጥርሶች፣ የራሴን ከናፍርት፣ የራሴን ዓይኖችና አፍንጫ፤ ብቻ መልኬን ማየት ክፉኛ ፈልጌያለሁ፡፡ በጣም ፈልጌያለሁ፡፡ አንዳንዴ ፊቴን ሳስበው፣ የተጨማደደ ቆዳ፣ ብነካው ለእጄ እንደቆረቆንዳ የሚሻክር፣ ከንፈርና ግራ ጉንጨ ላይ የሚያዳልጥ፣ ስፋቱ ስሙኒ የሚያህል ጠባሳ የሚኖረው ይመስለኛል፡፡ ግን በቀኝ እጄ ጣቶች ፊቴን ስዳስሰው፣ የሚያጋጥመኝ ሌላ ነው፡፡ እንደተባዘተ ጥጥ የሚለሰልስ ቆዳ!! የቆዳዬ ልሰላሴ ለራሴም ይደንቀኛል፡፡ የፊቴ ቆዳ የእኔ አይመስለኝም፡፡ እጄ የሌላ ሰው ፊት ላይ ያረፈ ነው የሚመስለኝ፡፡ ታዲያ ከራሴ ቆዳ ጋር በፍቅር የወደቅሁ ይመስለኛል፡፡ ደጋግሜ የቀኝ እጄን መዳፍ፣ ጉንጨ ላይ በቀስታ አንሸራትተዋለሁ፤ ጣፋጭ ደስታ እንደማር በውስጤ ሲፈስ ይሰማኛል፣ ጣቶቼ ምላስ ሆነው የቆዳዬን ወለላ የቀመሱ ዓይነት፡፡ የዓይኔን ሽፋሽፍት የቅንድቤን ለስላሳ ጸጉር በጣቶቼ ስዳሰሳቸው የሚሰማኝ ሐሴት ወደር የለውም፡፡ መልኬን እንደ ብሬል ፅሁፍ በጣቴ ነበር የማነበው፡፡ ከራሴ ጋር ፍቅር የጀመረኝ፣ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ ነበር፡፡ ምንም ይሁን ምን፣ መኖር ጥሩ ነው! “መኖር ምናባቱ!” ብለን በገዛ ፈቃዳችን ነፍሳችንን ከሥጋችን ለመለየት ፈራ ተባ ስንል፤ ሕይወት የተሰፋ ቅንጥጣቢዋን በኑሮ ጎዳናችን ላይ እየጣለች፥ እንደ ለማዳ ውሻ ታስከትለናለች፡፡ እንጅማ ገና መቼና መቼ የሰው ልጅ እራሱን አጥፍቶ፣ ይችን ዓለም ዳዋ በወረሳት ...