ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከኦክቶበር 15, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አምስቱ የለውጥ መሰትረቶች

https://Facebook.com/seidahmedH  አምስቱ የለውጥ መሠረቶች  #ለውጥ #ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን   1:-አስተሳሰብህን ለውጥ🌿💭    👉“የለውጥ ሁሉ መነሻና መሠረት የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን በውይይታችን በሰፊው አይተናል። ስኬታማ ግለሰቦች አስተሳሰባቸውን የመለወጥ፣ አመለካከታቸውን የመግራት፣ ዕይታቸውን የማስተካከልና አዕምሯቸውን የማዳበር ኃላፊነት ይወስዳሉ። ለዕውቀት ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ፤ ዕውቀት ወደነርሱ እስኪመጣ አይጠብቁም፤ እነርሱ ወደ ዕውቀት ይሄዳሉ፡፡ ያነብባሉ፤ ይጠይቃሉ፤ ይመራመራሉ። የአንድ ሰው ምግባር የአስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን ስለሚያውቁ _ ምግባራቸው ይስተካከል ዘንድ አዕምሯቸውን ይንከባከባሉ” አለና ንግግሩን አሳረገ። አዩብ ወደ ዳንኤል እየተመለከተ፡ 🖋️"Robin Sharma የተሰኘ ፀሐፊ 'A Man Who Sold His Ferrari በሚል መጽሐፉ ላይ አዕምሮን እንደ አትክልት ቦታ ይመስለዋል። የአንድ መኖሪያ ቤት አትክልት ቦታ በአግባቡ የሚኮተኮትና በየዕለቱ ውሃ የሚጠጣ፣ የተለያዩ የአበባ ዝርያዎች በሚያምር ሁኔታ የተተከሉበት እንደዚሁም ንጽሕናው የተጠበቀ ከሆነ፡- ያ የአትክልት ቦታ በጥሩ መዓዛ የሚያውድ እና ለዐይን ማራኪ በመሆኑ ከፍተኛ ሰላም እና ደስታ የሚሰጥ መዝናኛ ቦታ ይሆናል።🌿 🖋️በአንፃሩ ይህ የአትከልት ቦታ የቤት ጥራጊ ቆሻሻ የሚከማችበት እጣቢ የሚደፋበትና አንዳችም እንከብካቤ የማይደረግለት ከሆነ የቤቱ ባለቤትም ሆነ ሌላ ሰው ለዓይኑ የሚጸየፈውና አፍንጫውን ይዞ የሚያልፈው መጥፎ ቦታ ይሆናል። 👉የአንድ ግለሰብ አዕምሮም እንደዚሁ ነው። በተጨማሪም የአዕምሮ መዳበርና የአስተሳሰብ መስተካከል የሕይወታችንን ግብ በግልፅ እንድንገነዘብ ያስችለናል። ልናሳካ የምናልመ...