ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 15, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አንዲት የፅጌረዳ አበባ የባህር ዳር አበባ መሆን ከሞከረች

https://Facebook.com/seidahmedH https://seidahm.blogspot.com/2024/05/blog-post.html #ኦሾ  አንዲት የፅጌረዳ አበባ የባህር ዳር አበባ መሆን ከሞከረች፤ የባህር ዳር አበባ ደግሞ ፅጌረዳ አበባን ለመሆን ከጣረች፤ ፅጌረዳዋ የባህር ዳር አበባ መሆን ስለማትችል፤ የባህር ዳር አበባዋም ፅጌረዳን መሆን ስለማትችል ሁለቱም ከባድ ስቃይ ላይ ይወድቃሉ። ቢበዛ ሊያስመስሉ ይችላሉ። ማስመሰል ደግሞ የልብን የሚያደርስ አይደለም። የፅጌረዳ አበባ መሆን የምትችለው ፅጌረዳ አበባዋ ብቻ ናት። መጥፎው ነገር ደግሞ ፅጌረዳ አበባ የባህር ዳር አበባ ለመሆን በምታደርገው ሙከራ በከንቱ ጉልበቷን ማባከኗ ነው። የባህር ዳር አበባን መሆን አትችልም፣ ክህሎቱም የላትም። መሆንም አያስፈልጋትም። ተፈጥሮ የባህር ዳር አበባን ብትፈልግ ኖሮ የባህር ዳር አበባ ታደርጋት ነበር። ተፈጥሮ የፈለገችው ፅጌረዳ አበባን ነው። የፅጌረዳ አበባ የባህር ዳር አበባ ለመሆን በምታደርገው ሙከራ ሀይሏን በከንቱ ታባክናለች። ምናልባትም ከዚህ በኋላ ፅጌረዳ አበባንም ላትሆን ትችላለች። ፅጌረዳ አበባን የምትሆንበትን ሀይል ከየት ታገኛለች? ፅጌረዳ አበባን የምትሆንበትን ጥንካሬ ከየት ታገኛለች? ሁሉም ሰው በራሱ ልዩ ነው። ይህ በሚገባ መረዳት ያለባችሁ አስፈላጊ የሆነ ስነ-ልቦናዊ መርህ ነው። ከዚህ ቀደም አንድን ግለሰብ የመሰለ ሰው አልነበረም፤ ወደፊትም ከእሱ በኋላ ዳግም አይኖርም።  Seid Ahmed