ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ልጥፎች

ከኦክቶበር 19, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አምስቱ የለውጥ መሰረቶች ፪

https://Facebook.com/seidahmedH https://seidahm.blogspot.com/2024/05/blog-post.html #2  ኃላፊነት ውሰድ:- 💡 “የሕይወት ኃላፊነትን መውሰድ ወይም የራስ ተነሳሽነት ለግለሰብ ከዚያም አልፎ ለማኅበረሰብ ለውጥ ሁለተኛው መሠረት እንደሆነ አይተናል። ለሕይወቱ ሙሉ ኃላፊነት የወሰደ ግለሰብ ለውድቀቱ ውጫዊ ምክንያት በመስጠት ራሱን አይጥልም፤ ሌሎችን እየወቀሰ ራሱን ነፃ አያደርግም፤ ይልቁንስ የውድቀቱን ምክንያት አጥንቶ በማረም ለተሻለ ውጤት የመሥራት ኃላፊነት እንዳለበት ስለሚያውቅ ከወደቀበትበፍጥነት ይነሳል።🌿 💡በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዕድሎችን ይጠቀማል፤ ችግሮቹን ተቋቁሞ የተሻለ ማንነት ይገነባል” አለና ንግግሩን ገታ አደረገ።  በፈገግታ ታጅቦ ገለፃውን ቀጠለ። እኛም በፅሞና መከታተላችንን ቀጠልን፡-🌿 🖋️“በአንድ ወቅት ምን ሆነ መሰላችሁ?! አንድ ገበሬ ለዓመታት ያገለገለውን ፈረሱን እርጅና ስለተጫጫነው ሊያስወግደው ያስባል። ፈረሱን ሊጥለው ያሰበው የአካባቢው ነዋሪዎች ቆሻሻ ወደሚያከማቹበት መለስተኛ ጉድጓድ ውስጥ ነበር። የገበሬው ዕቅድ በሚጣለው ቆሻሻ ፈረሱ ታፍኖ ሕይወቱ እንዲያልፍና እዚያው ተቀብሮ እንዲቀር ማድረግ ነበር።  ገበሬው ፈረሱን የቆሻሻ ጉድጓዱ አፋፍ ድረስ እየጎተተ ወሰደና ወደ ጉድጓዱ ገፍትሮ ጣለው።🌿 🖋️ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው ፈረስ የመጀመሪያ ሥራ ከወደቀበት መነሳት ነበር። ከዚያም የሚሆነውን መጠባበቅ ጀመረ። የአካባቢው ነዋሪዎች በጆንያ ሞልተው የሚያመጡትን ቆሻሻ ወደ ጉድጓዱ ይዘረግፋሉ። ፈረሱ ጀርባው ላይ የሚያርፈውን የቆሻሻ ክምር አርገፍግፎ በመጣል እግሩ ሥር ያውለዋል። በመቀጠል እግሩ ሥር የተከመረው ቆሻሻ ላይ በመቆም ከፍታውን ይጨምራል።🌿...