ካህሊል ጅብራን
ተገዳይ በመገደሉ፣ተዘራፊውም በመዘረፍ
ከክፉ ተግባራት የነፃ አይሆንም፣
ጥፋተኛውም የተበዳዩ ተጠቂ ነውና
ይህንን ግዜ ከከተማው ዳኞች ኣንዱ ወደፊት ምጥቶ ቆመ፣ ኣለውም:- ስለ ወንጀልና ቅጣት ንገረን?"
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰለት:- በሌሎች ላይም ሆነ በእራሳችሁ ላይ ክፉ ስራ የሚትሰሩት መንፈሳችሁ በህዋው ውስጥ ሲዋልል ብቻችሁን ስትሆኑና ጠባቂ ሳይኖራቹ ስቀር ነው። ለዝያ ለተሰራ ሃጥያትም በቅዱሳን ደጅ ቆማቹ ማንም ሳያስተውላቹ በሩን ማንኳኳት እና ለጥቂት ግዜ መጠበቅ ይገባችኃል። ምክንያቱም ህሊናችሁ እንደ ውቅያኖስ ሰፊ ነውና። ሳይረክስም ለዘላለም ይቆያል........
...ህሊና እንደ ሰማዩ ሁሉ ባለክንፎችን ብቻ ክፉ ኣድርጎ ያነሳል።
ህሊናችሁ እንደ ፀሃይም ጭምር ነው። የፍልፈልን መንገዶችም አያውቅም። የእፍኝት ጉሬዎችንም አይፈልግም.....
ይሁንና ህሊናቹ በውስጣቹ ብቻውን አይኖርም።
በውስጣቹ ያለው አብዛኛው ክፍል ሰው ብሆንም የሚበዛው ኣሁንም ገና ሰው አልሆነም። ይሁንና በውስጣቹ የሚነቃበትን ግዜ ፍለጋ በእንቅልፍ ልቡ በጭጋግ ውስጥ የሚዘዋወር ቅርፀ ቢስ ድንክ ነው.....
አሁንም መናገር የምፈቅደው በውስጣቹ ስላለው ሰው ነው.....
ስለ ወንጀልና ስለወንጀል ቅጣትስ የሚያውቀው ያህሊናቹ ወይም ጭጋግ ውስጥ ያለው ድንክ ሳይሆን እርሱ እራሱ ውስጣችሁ አይደለምን?..... ብዙውን ግዜ ስለ ኣንድ በደልን የፈፀመ ሰው ስትናገሩ ሰውየው ከእናንተ ኣንዱ እንዳደለ ይልቅስ ለእናንተ እንግዳና ወደዓለማችሁ ዘው ብሎ የገባ ፍጡር እንደ ሆነ ኣድርጋቹ ስትናገሩ እሰማለው። እኔ ግን ቅዱሳንና ፃድቃንም ብሆኑ በያንዳንዳችሁ ውስጥ ካለው ከሁሉ ከፍ ከምለው ወጥተው ሊታዩ እንደ ማይችሉ ሁሉ ክፍዎችና ደካሞችም በውስጣችሁ ካለው ከሁሉ ዝቅ ከምለው የበለጠ ዝቅ ብለው ልወድቁ እንደማይችሉ እነግራችኃለው......
በተጨማሪ ከጠቅላላው ዛፍ እውቀት ውጭ ኣንዲት ቅጠል ብቻዋን ወደ ቢጫነት እንደ ማትለወጥ ሁሉ ክፉ አድራጊውም ቢሆን የእናንተን ሁሉ ድብቅ ፍላጎት ሳይኖር ክፉ ሊሰራ አይችሊም......
ልክ እንደ ሰልፈኛ ኣንድ ላይ ሆናቹ ነው ወደ ህሊናቹ የምትጓዙት። እናንተ መንገዱና የመንገዱ ተጓዦች ናቹ....
ከመሃከላቹ ኣንዳቹ ቁል ቁል ስትወድቁ የሚትወድቁት ከኋላችሁ ላሉት ከምንከባለለው ድንጋይ እንዲጠነቀቁ ስትሉ ነው........
ኣዎን የሚት ወድቁት ከፊታቹ ላሉትም ነው። ከፊታችሁ ያሉት ፈጣንና ተጠንቅቀው የሚራመዱ ብሆኑም የሚንከባለለውን ድንጋይ ከመንገዱ ላይ ሊያስወግዱት አልተቻላቸውምና ለነሱም ስትሉ ትወድቃላቹ.......
ምንም እንኳ ቃሉ ለልቦቻቹ ብከብዱም ይህን እነግራችኃለሁ:-
" ተገዳዩ ለገዛ እራሱ መገደል ከኃላፊነት አያመልጥም፣
"ተዘራፊውም በመዘረፉ ከተወቃሽነት አይድንም፣
" ፃድቅ የሆነው ሰውም ከክፉ ተግባራት የነፃ አይሆንም፣
" ከደሙ ንፁህ የሆነውም ወንጀለኛው ካደረጋቸው አድራጎቶች የፀዳ አይደለም......
ካህሊል ጅብራን
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ
Waaaw