ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

#አንተ_አባቴ_አይደለህም"

      "#አንተ#አባቴ#አይደለህም”

ከገባሁበት የሃሣብ ባሕር የወጣሁት ኡስታዝ ሉቅማን ስለ አዕምሮ በሰጡን ተጨማሪ ትንታኔ ነበር። ኡስታዙ አዕምሮን ማዳበርና ከስሜት (emotion) በላይ እንዲውል ማሰልጠን ያለውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው ሲያስረዱን፡-

“#አዕምሮን #በአግባቡ #አለመጠቀም #ስሜታዊና #ችኩል #ውሳኔዎች #እንድንወስን #ያደርገናል። የዳበረ አዕምሮ ያላቸው ስኬታማ ሰዎች በሚደርስባቸው ውጫዊ ጫና እና እነርሱ ለጫናው በሚሰጡት ምላሽ መካከል የማገናዘቢያ ጊዜ አላቸው፤ ድንገተኛና ችኩል ምላሽ አይሰጡም፤ ስለተፈጠረው ነገር ሙሉ መረጃ ሳይኖራቸው ለፍርድ አይሮጡም፤ ለውሳኔ አይቸኩሉም። ውሳኔያቸው ከዕውቀት እንጂ ከስሜት አይመነጭም። በስሜት ግፊት የተወሰነ ውሳኔ በአብዛኛው ከፍተኛ ጥፋት ያስከትላልና።” አሉ። ኡስታዙ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡

ከረጅም ጊዜ በፊት በአንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉ ምሁር ያቀረቡት አንድ አሳዛኝ ታሪክ ከላይ ያነሳሁላችሁን ሃሳብ ይበልጥ ግልፅ የሚያደርገው ይመስለኛል” አሉና ወደኛ ተመለከቱ።

የዛሬውን ውይይትም በዚሁ ታሪክ እናሳርግ" አሉ የዕለቱን ፕሮግራም ለማገባደድ በማሰብ። ታሪኩን ለመስማት ያለንን ጉጉት ከሁኔታችን ተረድተዋል። ኡስታዙ ታሪኩን እንዲህ ሲሉ አወጉን፡-

“ሰውየው ወደ ወህኒ ቤት የወረደው በጣም የምትወደውንና የሚወዳትን የትዳር አጋሩን ከአንድ ዓመት ሕፃን ልጁ ጋር በመተው ነበር። የአራት ዓመታት ጽኑ እሥራት ፍርደኛ ነው። እነኝህ ዓመታት ለባለቤቱ ፈታኝ ነበሩ። ቢሆንም በምትችለው አቅም ሁሉ የምታደርገውን እንክብካቤ አልቀነሰችም። ውድ ባለቤቷ ከእስሩ በላይ ሌላ ጭንቀት እንዳይፈጠርበት የአቅሟን ያህል ጥራለች። ምግብና ልብስ በማመላለስ ለባለቤቷ ያላትን አጋርነት አሳይታዋለች፣ የተሰበረ ሞራሉን ጠግናለታለች።

ባለቤቱ ሰውየው በታሰረበት የመጀመሪያ ዓመት ሕፃን ልጁን ወህኒ ቤት እያመጣች ታሳየው ነበር። በቀጣይ ዓመታት ግን መኖሪያ ቤታቸው ከወህኒ ቤቱ ርቆ

የሚገኝ በመሆኑ በየጊዜው ማመላለስ አልቻለችም ነበር። አባት ልጁን በየጊዜው ማግኘት ቢፈልግም ባለቤቱ ያለችበትን ሁኔታ በመገንዘቡ ብዙ አልተከፋም።

የባል ከእስር መፈቻ ዕለት ደርሷል። ሚስት በደስታ ተውጣ ወደ ወህኒ ቤት አመራች። ባሏን በፍቅርና በናፍቆት አቅፋ ሳመችው።

አልሐምዱ ሊላህ -እንኳን አላህ ለዚህ አበቃን ትላለች እንባ እየተናነቃት።

እርሱም ደጋግሞ አላህን ያመሰግናል። ቤቱ ደርሶ ልጁን እስኪያገኝ ቸኩሏል። ቤታቸው ደረሱ። መኖሪያ ቤታቸው የጋራ መኖሪያ ሕንፃ ውስጥ አራተኛ ፎቅ ላይ ነበር። ቤቱን ባለቤቱ በሚገባ አሰናድታ እንደጠበቀችው ሲያስተውል ደስታው ጨመረ። የናፈቀውን ልጁን አቅፎ እየሳመ የደስታ እንባው ኩልል አለ።

አባት ልጁን ጭኑ ላይ አስቀምጦ አገላብጦ ይስመዋል። ናፍቆቱ በቀላሉ የሚወጣለት አይመስልም፤ አሁንም አሁንም ልጁን ይስመዋል። ልጁ ግን የተለዬ ነገር አይታይበትም። አባት የአምስት ዓመት ሕፃን ልጁን፡

· እኔ'ኮ አባትህ ነኝ " ይለዋል - ዓይን ዓይኑን እየተመለከተ።

ሕፃኑ ፊቱን ቅጭም አደረገና፡- " አንተ አባቴ አይደለህም። የኔ አባት ማሚዬ ማታ ማታ አቅፋው የምትተኛው ሰውዬ ነው " ሲል ይመልስለታል።

አባት የሰማውን ማመን አልቻለም፤ ቀዝቃዛ ላብ በጀርባው ሲንቆረቆር ተሰማው ሰውነቱ በድን ሆነበት፤ ድንጋጤው ምላሱን አሳሰረው፤ የሚወዳት ባለቤቱ የፈፀመችበትን ከህደት መቋቋም ተሳነው፣ ከእስር በመፈታቱ የተሰማው ደስታ በንኖ ሲጠፋ ተሰማው። ይህ ሁሉ ሲሆን ባለቤቱ እርሱን ለመቀበል ያዘጋጀችውን ምግብ ለማቀራረብ ጓዳ ውስጥ ተፍ ተፍ በማለት ላይ ነበረች። የሰውየው ቁጣና እልህ ገደቡን ጥሶ ሊፈስ ተቃርቧል። የሚያደርገውን አጥቶ ይንቆራጠጣል። ሚስት ምግብ ይዛ ወደ ሳሎን ተመለሰች። ምግቡን ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጠች፡

የኔ ፍቅር አልሐምዱሊላህ : እንኳንም ተፈታህልኝ። የመጀመሪያ ፕሮግራማችን ዑምራ መሄድ ነው አይደል?' አለችው፡፡

ይሄኔ ባል ንዴቱ ይበልጥ ጨመረ፤ ሌላ የማስመሰል ሴራ ለማስተናገድ አልፈቀደም።

እንቺ አስመሳይ! ደግሞ ዑምራ እንሂድ ትይኛለሽ? ' አንባረቀባት።

በባሏ የባህሪ መቀያየር ግራ የተጋባችው ሚስት በድንጋጤ ድርቅ ብላ ቀረች። ልታረጋጋው እየሞከረች፡-

#ምነው #የኔ #ፍቅር?  አለች። * #የኔ #ፍቅር #አትበይኝ! !

የሰውየው ቁጣ እየናረ ሄደ። ከመቀመጫውው ተፈናጥሮ ተነሳ። ዓይኑን አፍጥጦ ተጠጋት። ሸሸችው። አሁንም ተጠጋት። ከቤት ወጥታ በረንዳ ጫፍ ላይ ቆመች። በከፍተኛ የስሜት ነውጥ ውስጥ ያለው ባል ምን ዓይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ኢያውቅም፤ አዕምሮው በስሜቱ ተሸፍኗል። በፍርሃት እየተርበደበደች ያለችውን ሚስቱን ቁልቁል ወደ ደረጃው በኃይል ገፈተራት። ሚዛኗን ስታ ወደቀች። በደረጃዎቹ ላይ ተንከባለለች። አሳዛኝ ሲቃ አሰምታ ራሷን ሳተች።

በንዴት ያበደው አባት የልጁን እናት አወዳደቅ እንኳ የሚያስተውልበት ጊዜ አላገኘም። በፍጥነት ወደ ሳሎን ቤት ተመለሰ። ሕፃን ልጁ ከፊት ለፊቱ ቆሟል። እናቱ ላይ የተፈጸመውን የማያውቀው ሕፃን በእጁ አንድ ነገር ይዟል።

" አባቴ ይሄ ሰውዬ ነው። ማሚዬ ማታ ማታ እቅፍ አድርጋው የምትተኛው አባቴ ይሄ ነው " አለ የአባቱን ፎቶ እያሳየው።

አባት ብርክ ያዘው፤ ፎቶው የርሱ የራሱ ነበር። ገፍትሮ ወደጣላት ባለቤቱ ተንደረደረ። መንደርደሩ ምን ሊፈይደው ሚስት ራሷን ስታ ተዘርርራለች፣ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ይዟት ነጎደ። ሕይወቷ ባያልፍም ሙሉ አካሏ ሽባ መሆኑን ሀኪሞች አረጋግጡ

ኡስታዝ ሉቅማን ትረካቸውን በሐዘን ተውጠው ቋጩ። ይህ ልባችንን የነካ አሳዛኝ ታሪክ ከየትኛውም ውሳኔ በፊት አዕምሯችንን ማሰራት እንዳለብን እስተማረን፣ ከስሜት በላይ ያልሆነ፣ ያልዳበረና ያልተረጋጋ ውሳኔ ምን ያህል አደጋ እንደሚያስከትል አስገነዘበን። ኡስታዙ

በሉ ልጆቼ፡ ለዛሬ እዚህ ላይ እናብቃ፡፡ ኢንሻአላህ በሚቀጥለው ሳምንት በዚሁ ሰዓት አንገናኛለን አሉና ዱዓእ አድርገውልን ፕሮግራሙን አጠናቀቁ።

አስተያየቶች

Seid Ahmed Hamid

የሀዘንን ጥበብ ተቀበል።

🌟👉 "ሀዘን ለደስታ ያዘጋጅሃል።  አዲስ ደስታ ለመግባት ቦታ እንዲያገኝ ሁሉንም ነገር ከቤትዎ በኃይል ጠራርጎ ይወስዳል።   👉ትኩስ አረንጓዴ ቅጠሎች በቦታቸው እንዲበቅሉ ከልባችሁ ቅርንጫፎች ቢጫ ቅጠሎችን ያናውጣል። 😇  👉የበሰበሱትን ሥሮች ይጎትታል፣ ስለዚህም ከታች የተደበቀ አዲስ ሥሮች ለማደግ ቦታ አላቸው።  ከልብህ የሚናወጠው ሀዘን ምንም ይሁን ምን እጅግ የተሻሉ ነገሮችን ይተካሉ።✨     ~ሩሚ~ 🌿🌸 የሀዘንን ጥበብ መቀበል 🌸🌿  ሀዘን የሽንፈት ምልክት ሳይሆን የለውጥ አብሳሪ ነው።  አዲስ ደስታ እንዲያብብ መንገዱን ያጸዳል፣ አሮጌውን በማውጣት ለአዲስ ደስታ ቦታ ይሰጣል።  የበልግ ንፋስ ቅጠሉን እንደሚያናውጥ ሀዘንም ልባችንን ያናውጣል አዲስ ጅምር እና ጥልቅ እድገት።  ሀዘንን እንደ የመታደስ ምንጭ እንቀበል እና በህይወት ገነት ውስጥ ለሚጠብቀን ታላቅ ደስታ መንገዱን እንንጥረግ።  🌼💚  #ሀዘንን ተቀበል #በለውጥ ውስጥ ደስታን አግኝ #አዲስ ጅምር #የእድገት አስተሳሰብ Facebook.com/Seid.Ahmed1111

ካህሊል ጅብራን

  ካህሊል ጅብራን ተገዳይ በመገደሉ፣ተዘራፊውም በመዘረፍ ከክፉ ተግባራት የነፃ አይሆንም፣ ጥፋተኛውም የተበዳዩ ተጠቂ ነውና ይህንን ግዜ ከከተማው ዳኞች ኣንዱ ወደፊት ምጥቶ ቆመ፣ ኣለውም:- ስለ ወንጀልና ቅጣት ንገረን?" እርሱም እንዲህ ሲል መለሰለት:- በሌሎች ላይም ሆነ በእራሳችሁ ላይ ክፉ ስራ የሚትሰሩት መንፈሳችሁ በህዋው ውስጥ ሲዋልል ብቻችሁን ስትሆኑና ጠባቂ ሳይኖራቹ ስቀር ነው። ለዝያ ለተሰራ ሃጥያትም በቅዱሳን ደጅ ቆማቹ ማንም ሳያስተውላቹ በሩን ማንኳኳት እና ለጥቂት ግዜ መጠበቅ ይገባችኃል። ምክንያቱም ህሊናችሁ እንደ ውቅያኖስ ሰፊ ነውና። ሳይረክስም ለዘላለም ይቆያል........ ...ህሊና እንደ ሰማዩ ሁሉ ባለክንፎችን ብቻ ክፉ ኣድርጎ ያነሳል። ህሊናችሁ እንደ ፀሃይም ጭምር ነው። የፍልፈልን መንገዶችም አያውቅም። የእፍኝት ጉሬዎችንም አይፈልግም..... ይሁንና ህሊናቹ በውስጣቹ ብቻውን አይኖርም። በውስጣቹ ያለው አብዛኛው ክፍል ሰው ብሆንም የሚበዛው ኣሁንም ገና ሰው አልሆነም። ይሁንና በውስጣቹ የሚነቃበትን ግዜ ፍለጋ በእንቅልፍ ልቡ በጭጋግ ውስጥ የሚዘዋወር ቅርፀ ቢስ ድንክ ነው..... አሁንም መናገር የምፈቅደው በውስጣቹ ስላለው ሰው ነው..... ስለ ወንጀልና ስለወንጀል ቅጣትስ የሚያውቀው ያህሊናቹ ወይም ጭጋግ ውስጥ ያለው ድንክ ሳይሆን እርሱ እራሱ ውስጣችሁ አይደለምን?..... ብዙውን ግዜ ስለ ኣንድ በደልን የፈፀመ ሰው ስትናገሩ ሰውየው ከእናንተ ኣንዱ እንዳደለ ይልቅስ ለእናንተ እንግዳና ወደዓለማችሁ ዘው ብሎ የገባ ፍጡር እንደ ሆነ ኣድርጋቹ ስትናገሩ እሰማለው። እኔ ግን ቅዱሳንና ፃድቃንም ብሆኑ በያንዳንዳችሁ ውስጥ ካለው ከሁሉ ከፍ ከምለው ወጥተው ሊታዩ እንደ ማይችሉ ሁሉ ክፍዎችና ደካሞችም በውስጣችሁ ካለው ከሁሉ ...

Posative thinking

  "#አንዴ" #ኣንድ #ትልቅ #ፕሮፌሰር #ተወዳጅ #ዑስታዝ ከአንድ ተውዳጅ ታማሪው ጋር ግቢ ውስጥ ወክ ያደርጋሉ። እሄም ወክ ስላልበቃቸው ከዩኒቨርሲቲው ጀርባ ወዳሉ መንደሮች እንደገና ለመንቀሳቀስ ወሰኑ። ወሬዎቹን እየተጫወቱ ስለ ህይዎት መንገድ ቀጠሉ። ትንሽም እንደ ተጓዙ መንገድ ላይ ልብሶቹን አወላልቆ ቦት ጫማቸውን አውልቆ ስራ ሚሰራን የቀን ሰራተኛን ተመለከቱ። ከዝያ ወጣቱ ለመምህሩ፣ ምን ኣለው....ተመልከት  እሄን ጫማ እኔ ሰርቀዋለው፣ እሄን ሰው ሰርቀውና ስራ ጨርሶ ዞር ሲል፣ጫማው ሲጠፋው እንዴት እንደምሆን ትመለከተዋለህ "እንስቃለን"ኣለው። እሄን ሲለው መምህሩ እሄን ወጣት የህይዎት ሜዳ ላይ ማስተማር የሚችልበት ጥሩ አጋጣሚ ኣገኘ። እችን ሀሳብ ቶሎ ለቀም ኣረጋትና፣ እንዲህ ብንገለብጠውስ አለው። እይታውን እየገለበጠለት ነው። ሰውየው ጫማው ጠፍቶት ሲጮህ ፣ሲያለቅስ፣ ሲጨነቅ አይተን ከምንስቅ፣ የሆኑ ሳንቲሞች ጫማው ውስጥ እንክተትና ሳያስበው ሳንቲሞቹን ስያወጣ፣ ሚፈጠርበትን ደስታ አይተን ብንስቅ አይሻልም? አለው። "ወጣቱ" ሀሳቡ እንግዳ ብሆንበትም ሀሳቡን ወደደው። ያንኛውን ተንኮል ሚመስለውን ስራ ኖሮበታል፣ ቅንነትን ነው ያልኖረበት፣ ልሞክረው ኣለ፣ እይታው እየተስተካከለ ነው። Attitudዱ እያደገ ነው እሄ ሰው። እሺ አለ፣  ኪስህ ስንት ኣለ አወጣጠ ሳንትሞች ብሮች፣ መምህሩም አወጡ ጫማው ውስጥ ጨመሩት። ከዚያም ራቅ ብሎ ጥላ ውስጥ ቁጭ ብለው ሰወየው ስራ እስኪጨርስ ጠበቁ። ሰውየውም ስራውን ጨረሰ፣ እጆቹን ታጠብ፣ እግሮቹን ታጠበ፣ ልብሱን ኣራገፍ፣ ያወለቀውን ልብስ ቀየረ፣ ኮፍያውን ደረበ ኣሁን ምን ቀረው? "ጫማው፣" ...ጫማውን ሊለብስ ብድግ አደረገና ድንገት የሆነ ነገር ገብቶበት...