#2 ኃላፊነት ውሰድ:-
💡“የሕይወት ኃላፊነትን መውሰድ ወይም የራስ ተነሳሽነት ለግለሰብ ከዚያም አልፎ ለማኅበረሰብ ለውጥ ሁለተኛው መሠረት እንደሆነ አይተናል። ለሕይወቱ ሙሉ
ኃላፊነት የወሰደ ግለሰብ ለውድቀቱ ውጫዊ ምክንያት በመስጠት ራሱን አይጥልም፤ ሌሎችን እየወቀሰ ራሱን ነፃ አያደርግም፤ ይልቁንስ የውድቀቱን ምክንያት አጥንቶ
በማረም ለተሻለ ውጤት የመሥራት ኃላፊነት እንዳለበት ስለሚያውቅ ከወደቀበትበፍጥነት ይነሳል።🌿
💡በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዕድሎችን ይጠቀማል፤ ችግሮቹን ተቋቁሞ የተሻለ ማንነት ይገነባል” አለና ንግግሩን ገታ አደረገ።
በፈገግታ ታጅቦ ገለፃውን ቀጠለ። እኛም በፅሞና
መከታተላችንን ቀጠልን፡-🌿
🖋️“በአንድ ወቅት ምን ሆነ መሰላችሁ?! አንድ ገበሬ ለዓመታት ያገለገለውን ፈረሱን እርጅና ስለተጫጫነው ሊያስወግደው ያስባል። ፈረሱን ሊጥለው ያሰበው የአካባቢው ነዋሪዎች ቆሻሻ ወደሚያከማቹበት መለስተኛ ጉድጓድ ውስጥ ነበር።
የገበሬው ዕቅድ በሚጣለው ቆሻሻ ፈረሱ ታፍኖ ሕይወቱ እንዲያልፍና እዚያው ተቀብሮ እንዲቀር ማድረግ ነበር።
ገበሬው ፈረሱን የቆሻሻ ጉድጓዱ አፋፍ ድረስ እየጎተተ ወሰደና ወደ ጉድጓዱ ገፍትሮ ጣለው።🌿
🖋️ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው ፈረስ የመጀመሪያ ሥራ ከወደቀበት መነሳት ነበር። ከዚያም የሚሆነውን መጠባበቅ ጀመረ። የአካባቢው ነዋሪዎች በጆንያ ሞልተው
የሚያመጡትን ቆሻሻ ወደ ጉድጓዱ ይዘረግፋሉ። ፈረሱ ጀርባው ላይ የሚያርፈውን የቆሻሻ ክምር አርገፍግፎ በመጣል እግሩ ሥር ያውለዋል። በመቀጠል እግሩ ሥር
የተከመረው ቆሻሻ ላይ በመቆም ከፍታውን ይጨምራል።🌿
🖋️የአካባቢው ነዋሪዎች የቆሻሻከምር ወደ ጉድጓዱ መጣላቸውን ቀጥለዋል፤ እርሱም ከጀርባው ላይ በማርገፍገፍ ከእግሩ ስር በማድረግ ከፍታውን ይጨምራል። በዚህ መልኩ የሚጫነውን ቆሻሻ
እያርገፈገፈ እንደመሰላል በመጠቀም ከጉድጓዱ አፋፍ ላይ ወጥቶ ተገኘ፡” አለና ንግግሩን ቋጨ፡፡🌿
ዓማር ቀበል አደረገና፡-
💡“ግሩም ምሳሌ ነው የነገርከን መገርሳ። የራስ ተነሳሽነት ባሕሪይ ያላቸው ግለሰቦች በደረሰባቸው ችግር በማማረር ብቻ ተውጠው ችግሮቹ አፍነው እንዲገድሏቸው አይፈቅዱም፤ በችግሮቹ ውስጥ መፍትሄ ይዘይዳሉ። ከአስቸጋሪና መጥፎ ሁኔታ ለመውጣት የራስ ተነሳሽነት ባሕሪይ ወሳኝ የመሆኑን ያህል ካለንበት መልካም ሁኔታም ወደተሻለ ለመለወጥ ይኸው ባሕሪ ያስፈልገናል" ሲል ተጨማሪ ሃሳብ አከለ።🌿
#ለውጥ #ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን #ድንቅ_ጥቅሶች #Wonderful_Qoute
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
facebook.com/seidahmedH
3- ህመሙን ተቋቋም:-እንቀጥላለን
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ
Waaaw