ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

ጣቶቹ

ቆንጆ ነኝ ወይስ አይደለሁም? የሚል ጥያቄ ድንገት አእምሮዬ ውስጥ ብለጭ ያለው፣ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ ነበር፡፡ እስከዛሬም በየቀኑ፣ በየሰዓቱ፣ ጥያቄው በውስጤ ያቃጭላል፡፡ አንዳንዴ እንዲያውም የሆነ ሰው ጠርቼ “ለመሆኑ ቆንጆ ነኝ ወይስ _ አይደለሁም? ብዬ መጠየቅ ያምረኛል፡፡ የራሴን ፊት ማየት ናፍቄያለሁ:: የራሴን ፈገግታ፣ የራሴን ጥርሶች፣ የራሴን ከናፍርት፣ የራሴን ዓይኖችና አፍንጫ፤ ብቻ መልኬን ማየት ክፉኛ ፈልጌያለሁ፡፡ በጣም ፈልጌያለሁ፡፡ አንዳንዴ ፊቴን ሳስበው፣ የተጨማደደ ቆዳ፣ ብነካው ለእጄ እንደቆረቆንዳ የሚሻክር፣ ከንፈርና ግራ ጉንጨ ላይ የሚያዳልጥ፣ ስፋቱ ስሙኒ የሚያህል ጠባሳ የሚኖረው ይመስለኛል፡፡ ግን በቀኝ እጄ ጣቶች ፊቴን ስዳስሰው፣ የሚያጋጥመኝ ሌላ ነው፡፡ እንደተባዘተ ጥጥ የሚለሰልስ ቆዳ!! የቆዳዬ ልሰላሴ ለራሴም ይደንቀኛል፡፡ የፊቴ ቆዳ የእኔ አይመስለኝም፡፡ እጄ የሌላ ሰው ፊት ላይ ያረፈ ነው የሚመስለኝ፡፡ ታዲያ ከራሴ ቆዳ ጋር በፍቅር የወደቅሁ ይመስለኛል፡፡ ደጋግሜ የቀኝ እጄን መዳፍ፣ ጉንጨ ላይ በቀስታ አንሸራትተዋለሁ፤ ጣፋጭ ደስታ እንደማር በውስጤ ሲፈስ ይሰማኛል፣ ጣቶቼ ምላስ ሆነው የቆዳዬን ወለላ የቀመሱ ዓይነት፡፡ የዓይኔን ሽፋሽፍት የቅንድቤን ለስላሳ ጸጉር በጣቶቼ ስዳሰሳቸው የሚሰማኝ ሐሴት ወደር የለውም፡፡ መልኬን እንደ ብሬል ፅሁፍ በጣቴ ነበር የማነበው፡፡ ከራሴ ጋር ፍቅር የጀመረኝ፣ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ ነበር፡፡ ምንም ይሁን ምን፣ መኖር ጥሩ ነው! “መኖር ምናባቱ!” ብለን በገዛ ፈቃዳችን ነፍሳችንን ከሥጋችን ለመለየት ፈራ ተባ ስንል፤ ሕይወት የተሰፋ ቅንጥጣቢዋን በኑሮ ጎዳናችን ላይ እየጣለች፥ እንደ ለማዳ ውሻ ታስከትለናለች፡፡ እንጅማ ገና መቼና መቼ የሰው ልጅ እራሱን አጥፍቶ፣ ይችን ዓለም ዳዋ በወረሳት ነበር፡፡ መኖር ትልቅ ሱስ ነው፡፡ ይኼው ወፈሰማይ የኑሮ ሱሰኛ የዕድሜ ሲጋራውን ለኩሶ፣ የመኖር ሱሱን ሊያሷርፍ በአፍና በአፍንጫው ተስፋን ይምጋታል፡፡ አዲስ ዛሬን ወደ ውስጡ እየሳበ የተቃጠለ ትላንቱን ወደ ውጭ ይተነፍሰዋል፡፡ ለዚያ ይሆን እንዴ አየሩ ነበር ነበር የሚሸተው? የሚበዛው ሰው ልከ እንደሲጋራ ርጋፊውን የታሪከ ወጭቱ ላይ እየተረኮሰ፣ የነገ ጀምበሩን በጉጉት ሲጠብቅ እጁ ላይ ዕድሜ ተቃጥላ ትከስማለች፡፡ ቢሆንም መኖር ያሳሳል፡፡ እግዜር መቼም ከአንድ ዓመት በፊት “ግደለኝ” እያልኩ ደጋግሜ የጸለይኩትን ጸሎት ሰምቶ፣ አሁን ከተፍ ቢልና “ልጄ! በይ ተነሽ እንሂድ” ቢለኝ “ቀልድ አታውቅም እንዴ!” የምለው ይመስለኛል፡፡ መኖር ያሳሳኝ ከጀመረ፣ አንድ ዓመት አካባቢ ሆነኝ:: ከሰኞ እስከ ዓርብ ድረስ መንደሩ ላይ ከባድ ዝምታ ይረብበታል፡፡ ሕፃናት ትምህርት ቤት፣ አዋቂዎችም ወደየሥራቸው ይሄዳሉ፡፡ ሥራ የሌላቸው ጠራራውን ሸሸት በየቤታቸው ስለሚከተቱ፣ የሰው ድምፅ አይሰማም፡፡ ከቅርብ ርቀት (ሰፈራችን ካለው ትዝታ ሙዚቃ ቤት የሚባል የተከፈተ) ሱዳንኛ ዘፈን ይሰማኛል፡፡ ሱዳንኛ ዘፈን ስሰማ፣ አገሩ በረሃ የሆነ ነው የሚመስለኝ፡፡ሁሉም ሰው ትቶኝ ወደሆነ አገር የተሰደደና ብቻዬን የቀረሁ እየመሰለኝ እፈራለሁ፡፡ አለ አይደል፣ ሁሉም ሰው እኔ ሳልሰማ በምልክት እና በጥቅሻ ተጠራርቶ ወደ ሱዳን የተሰደደ “ሳትሰማን እንሂድ፣ እሷን ማን ይጎትታል! እየተባባለ እግሬ አውጭኝ ያለ፡፡ (የሚያወጣ እግር ያላቸው) ታዲያ እንዲህ ሰፈሩ ጭር ሲል፣ ሁሉም ሰው ትቶኝ ወደሆነ አገር የሄደ እየመሰለኝ መፍራት ከጀመርኩ፣ አንድ ዓመት አካባቢ ሆነኝ፡፡ የሰፈሩን ሰው ሁሉ በስም እየጠራሁ “አላችሁ ወይ?” “ማለት ያምረኛል ፡፡ “እስቲ ካላችሁ .ጣታችሁን አሳዩኝ! በፊት በፊት ይኼን ዝምታ አልወደውም ነበር፡፡ ስልችት ነበር የሚለኝ፡፡ አሁን ግን ዝምታው እንደነፍስ ሙዚቃ፣ ከሩቅ እንደሚሰማ ኅብረ-ዝማሬ ሆኖ ውስጤን በደስታ ያፍነከንከዋል፡፡ ተፍነክንኬ ሳላበቃ ደግሞ፣ ውስጤን በድንጋጤ ትርክክ የሚያደርግ ስጋት ይፈጠራል፡፡ ደስታውም ሆነ ድንጋጤው የሚነዝር ነገር አለው፡፡ (ሰዎች ሲያወሩ ከእግር ጥፍሬ እስከእራስ ፀጉሬ ነዘረኝ እንደሚሉት) “የደስታሽም ሆነ የድንጋጤሽ መነሻ ምንድነው?” ብባል መልስ የለኝም፡፡ ከመሬት ተነስቼ መደሰትና፣ ከመሬት ተነስቼ መደንገጥ ከጀመርኩ፣ አንድ ዓመት አካባቢ ሆነኝ፡፡ #አጽናፍ ነው ስሜ፣ አፅናፍ ብሎ ስም ያወጣልኝ ማን እንደሆነ እግዜር ይወቅ፡፡ ምናልባት እናቴ፣ አባቴ፣ ወይም አንዱ መንገደኛ ይሆናል፡፡ ዞሮ ዞሮ ስሜን ያወጣው ሰው በከንቱ ደከመ፡፡ ማንም በዚህ ስም ጠርቶኝ አያውቅም፡፡ በስሜ መጠራት ይናፍቀኛል፡፡ “አጽናፍ

አስተያየቶች

አስተያየት ይለጥፉ

Waaaw

Seid Ahmed Hamid

የሀዘንን ጥበብ ተቀበል።

🌟👉 "ሀዘን ለደስታ ያዘጋጅሃል።  አዲስ ደስታ ለመግባት ቦታ እንዲያገኝ ሁሉንም ነገር ከቤትዎ በኃይል ጠራርጎ ይወስዳል።   👉ትኩስ አረንጓዴ ቅጠሎች በቦታቸው እንዲበቅሉ ከልባችሁ ቅርንጫፎች ቢጫ ቅጠሎችን ያናውጣል። 😇  👉የበሰበሱትን ሥሮች ይጎትታል፣ ስለዚህም ከታች የተደበቀ አዲስ ሥሮች ለማደግ ቦታ አላቸው።  ከልብህ የሚናወጠው ሀዘን ምንም ይሁን ምን እጅግ የተሻሉ ነገሮችን ይተካሉ።✨     ~ሩሚ~ 🌿🌸 የሀዘንን ጥበብ መቀበል 🌸🌿  ሀዘን የሽንፈት ምልክት ሳይሆን የለውጥ አብሳሪ ነው።  አዲስ ደስታ እንዲያብብ መንገዱን ያጸዳል፣ አሮጌውን በማውጣት ለአዲስ ደስታ ቦታ ይሰጣል።  የበልግ ንፋስ ቅጠሉን እንደሚያናውጥ ሀዘንም ልባችንን ያናውጣል አዲስ ጅምር እና ጥልቅ እድገት።  ሀዘንን እንደ የመታደስ ምንጭ እንቀበል እና በህይወት ገነት ውስጥ ለሚጠብቀን ታላቅ ደስታ መንገዱን እንንጥረግ።  🌼💚  #ሀዘንን ተቀበል #በለውጥ ውስጥ ደስታን አግኝ #አዲስ ጅምር #የእድገት አስተሳሰብ Facebook.com/Seid.Ahmed1111

ካህሊል ጅብራን

  ካህሊል ጅብራን ተገዳይ በመገደሉ፣ተዘራፊውም በመዘረፍ ከክፉ ተግባራት የነፃ አይሆንም፣ ጥፋተኛውም የተበዳዩ ተጠቂ ነውና ይህንን ግዜ ከከተማው ዳኞች ኣንዱ ወደፊት ምጥቶ ቆመ፣ ኣለውም:- ስለ ወንጀልና ቅጣት ንገረን?" እርሱም እንዲህ ሲል መለሰለት:- በሌሎች ላይም ሆነ በእራሳችሁ ላይ ክፉ ስራ የሚትሰሩት መንፈሳችሁ በህዋው ውስጥ ሲዋልል ብቻችሁን ስትሆኑና ጠባቂ ሳይኖራቹ ስቀር ነው። ለዝያ ለተሰራ ሃጥያትም በቅዱሳን ደጅ ቆማቹ ማንም ሳያስተውላቹ በሩን ማንኳኳት እና ለጥቂት ግዜ መጠበቅ ይገባችኃል። ምክንያቱም ህሊናችሁ እንደ ውቅያኖስ ሰፊ ነውና። ሳይረክስም ለዘላለም ይቆያል........ ...ህሊና እንደ ሰማዩ ሁሉ ባለክንፎችን ብቻ ክፉ ኣድርጎ ያነሳል። ህሊናችሁ እንደ ፀሃይም ጭምር ነው። የፍልፈልን መንገዶችም አያውቅም። የእፍኝት ጉሬዎችንም አይፈልግም..... ይሁንና ህሊናቹ በውስጣቹ ብቻውን አይኖርም። በውስጣቹ ያለው አብዛኛው ክፍል ሰው ብሆንም የሚበዛው ኣሁንም ገና ሰው አልሆነም። ይሁንና በውስጣቹ የሚነቃበትን ግዜ ፍለጋ በእንቅልፍ ልቡ በጭጋግ ውስጥ የሚዘዋወር ቅርፀ ቢስ ድንክ ነው..... አሁንም መናገር የምፈቅደው በውስጣቹ ስላለው ሰው ነው..... ስለ ወንጀልና ስለወንጀል ቅጣትስ የሚያውቀው ያህሊናቹ ወይም ጭጋግ ውስጥ ያለው ድንክ ሳይሆን እርሱ እራሱ ውስጣችሁ አይደለምን?..... ብዙውን ግዜ ስለ ኣንድ በደልን የፈፀመ ሰው ስትናገሩ ሰውየው ከእናንተ ኣንዱ እንዳደለ ይልቅስ ለእናንተ እንግዳና ወደዓለማችሁ ዘው ብሎ የገባ ፍጡር እንደ ሆነ ኣድርጋቹ ስትናገሩ እሰማለው። እኔ ግን ቅዱሳንና ፃድቃንም ብሆኑ በያንዳንዳችሁ ውስጥ ካለው ከሁሉ ከፍ ከምለው ወጥተው ሊታዩ እንደ ማይችሉ ሁሉ ክፍዎችና ደካሞችም በውስጣችሁ ካለው ከሁሉ ...

Posative thinking

  "#አንዴ" #ኣንድ #ትልቅ #ፕሮፌሰር #ተወዳጅ #ዑስታዝ ከአንድ ተውዳጅ ታማሪው ጋር ግቢ ውስጥ ወክ ያደርጋሉ። እሄም ወክ ስላልበቃቸው ከዩኒቨርሲቲው ጀርባ ወዳሉ መንደሮች እንደገና ለመንቀሳቀስ ወሰኑ። ወሬዎቹን እየተጫወቱ ስለ ህይዎት መንገድ ቀጠሉ። ትንሽም እንደ ተጓዙ መንገድ ላይ ልብሶቹን አወላልቆ ቦት ጫማቸውን አውልቆ ስራ ሚሰራን የቀን ሰራተኛን ተመለከቱ። ከዝያ ወጣቱ ለመምህሩ፣ ምን ኣለው....ተመልከት  እሄን ጫማ እኔ ሰርቀዋለው፣ እሄን ሰው ሰርቀውና ስራ ጨርሶ ዞር ሲል፣ጫማው ሲጠፋው እንዴት እንደምሆን ትመለከተዋለህ "እንስቃለን"ኣለው። እሄን ሲለው መምህሩ እሄን ወጣት የህይዎት ሜዳ ላይ ማስተማር የሚችልበት ጥሩ አጋጣሚ ኣገኘ። እችን ሀሳብ ቶሎ ለቀም ኣረጋትና፣ እንዲህ ብንገለብጠውስ አለው። እይታውን እየገለበጠለት ነው። ሰውየው ጫማው ጠፍቶት ሲጮህ ፣ሲያለቅስ፣ ሲጨነቅ አይተን ከምንስቅ፣ የሆኑ ሳንቲሞች ጫማው ውስጥ እንክተትና ሳያስበው ሳንቲሞቹን ስያወጣ፣ ሚፈጠርበትን ደስታ አይተን ብንስቅ አይሻልም? አለው። "ወጣቱ" ሀሳቡ እንግዳ ብሆንበትም ሀሳቡን ወደደው። ያንኛውን ተንኮል ሚመስለውን ስራ ኖሮበታል፣ ቅንነትን ነው ያልኖረበት፣ ልሞክረው ኣለ፣ እይታው እየተስተካከለ ነው። Attitudዱ እያደገ ነው እሄ ሰው። እሺ አለ፣  ኪስህ ስንት ኣለ አወጣጠ ሳንትሞች ብሮች፣ መምህሩም አወጡ ጫማው ውስጥ ጨመሩት። ከዚያም ራቅ ብሎ ጥላ ውስጥ ቁጭ ብለው ሰወየው ስራ እስኪጨርስ ጠበቁ። ሰውየውም ስራውን ጨረሰ፣ እጆቹን ታጠብ፣ እግሮቹን ታጠበ፣ ልብሱን ኣራገፍ፣ ያወለቀውን ልብስ ቀየረ፣ ኮፍያውን ደረበ ኣሁን ምን ቀረው? "ጫማው፣" ...ጫማውን ሊለብስ ብድግ አደረገና ድንገት የሆነ ነገር ገብቶበት...