ወደ ዋና ይዘት ዘለው ይሂዱ

የፀሎት ምላሽ

http://seidahm.blogspot.com https://seidahm.blogspot.com/2024/05/blog-post.htmlhttps://t.me/WonderfulQoute/422

አንድ ሰው እንዲህ ሲል ልምምዱን ያካፍለናል፡- 
“ፈጣሪን ጥንካሬ እንዲሰጠኝ ጠየኩት፣ 
ፈጣሪም ጠንካራ የሚያደርጉኝን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሰጠኝ . . . 
🌟ጥበብን እንዲሰጠኝ ጠየኩት፣ 
👉እሱም የምፈታቸውን ችግሮች ሰጠኝ . . . 
🌟ድፍረት እንዲሰጠኝ ጠየኩት፣ 
👉እሱም ተጋፍጬ የማሸንፋቸውን አደገኛ ነገሮች ሰጠኝ . . . 
❣️ፍቅርን እንዲጠኝ ጠየኩት፣ 
👉እሱም እንድረዳቸው የተቸገሩ ሰዎችን ሰጠኝ . . . በጊዜው ግር ቢለኝም ጸሎቴ እንደተመለሰ የገባኝ የኋላ ኋላ ነው፡፡🙏🙏🙏

 🙏 አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ካላችሁ፣ ጠንካራ ሆናችሁ እንደምትወጡ ላስታውሳችሁ፡፡ 
🙏 ለመፍታት አስቸጋሪ የሆኑ ሁኔታዎች ከተደራረቡባችሁ፣ 🌟ጥበበኛ ወደመሆን እንደምታድጉ ላሳስባችሁ፡፡ 
👉 የግድ አደገኛ ነገሮችን የመጋፈጥ ግዴታ ውስጥ የምታልፉ ከሆነ፣ 🙏ደፋርነት እያዳበራችሁ  እንደምትሄዱ  ጥርጥር አይግባችሁ፡፡ 
👉በብዙ ችግር የተጎሳቆሉ ሰዎች እየተጠጓችሁ እንደሆነ ካያችሁ፣ ✍️የፍቅርና የርህራሄ  ጉዳይ  እየተለማመዳችሁ እንደምትሄዱ ትዝ ይበላችሁ፡፡☀️🌹🏵️
facebook.com/seidahmedH

አስተያየቶች